You are here: Skip Navigation LinksFeMSEDA Web Portal

 

FeMSEDA Web Portal
 
========================================
የካይዘን ስልጠና ሰነዶች ለማውረድ እዚህ ይጫኙ ========================================

(ጥቅምት 03፣ 2007 ዓ.ም) - የሰንደቅ አላማችንን ክብር ለመጠበቅ ድህነት ላይ ጀመርነውን ትግል አጠናክረን መቀተል እንደሚገባ ተገለጸ

የፌዴራል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤጀንሲ አመራርና ሰራተኞች ‹‹በሕዝቦችዋ ተሳትፎና ትጋት ድህነትን ድል በመንሳት ብሔራዊ ክብርዋንና ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ በማድረግ ላይ ያለች ሀገር! ኢትዮጵያ!›› በሚል መሪ ቃል 7ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ አከበሩ፡፡

የፌዴራል ኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረመስቀል ጫላ በዝግጅቱ ላይ እንደገለጹት ከረጅም ዓመታት በፊት በስልጣኔዋ ትታወቅ የነበረችው አገራችን በድህነት አዘቅት ውስጥ ተዘፍቃ በመቆየቷ ብሔራዊ ክብሯ ላይ አሉታዊ ገጽታ ፈጥሮ የቆየ እንደነበር አስታውሰው ካለፉት 24 ዓመታት ወዲህ ግን ወደ እድገት ጎዳና የሚያመራትን ትክክለኛ የልማት መንገድ መርጣ በመጓዟ እምርታዊ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ እንደምትገኝ ጠቅሰዋል፡፡


< አያይዘውም ከድህነት በላይ የሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ ክብር ዝቅ የሚያደርግ ጉዳይ ባለመኖሩም ይህ ትውልድ በድህነት ላይ በሚደረገው ዘመቻ ግንባር ቀደም ሚናውን በመጫወት የሀገራችንን ህዳሴ የማረጋገጥ ታሪካዊ አደራ የተጣለበ ት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በተለይም በድህነት ትግሉ ቁልፉን ተልዕኮ በወሰደው በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ የተሰማራን አካላት የዜጎቻችንን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ወሳኙን ሚና መጫወት የሚጠበቅብን ሲሆን የዛሬው ዕለትም የሰንደቅ ዓላማ እሴቶቻችንን የበለጠ ለማጎልበትና ጠንክረን ለመስራት ቃል የምንገባበት ቀን ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል። የሰንደቅ ዓላማ ሁላችንም እንደምንጠራበት ስያሜ ሁሉ አገራችን የምትወከልበት መለያ እንደሆነና አገራችንም እንደ አገር ተደማጭነት የሚኖራት ከድህነት ጋር በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ ተወጥቶ የተሻለ ደረጃ ላይ ስትደርስ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡በዕለቱም የሰንደቅ ዓላማ ቀንን በማስመልከት የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አማካኝነት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ስነ-ስርዓት ከተከናወነ በኋላ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል፡፡ _________________________________________

(ጥቅምት 2፣ 2007 ዓ/ም) - ከካይዘን ፍልስፍና መለያዎች መካከል አንዱ አስቀድሞ ሰራተኛውን ብቁ ማድረግ መሁኑ ተገለጸ

የፌ/ጥ/አ/ኢ/ል/ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከፌዴራል ኤጀንሲውና ከክልሎች የተውጣጡ ከ180 በላይ ተሳታፊዎች የተካፈሉበት የካይዘን ፍልስፍናን የተመለከተ ስልጠና በአዳማ ከተማ ተሰጠ:: ካይዘን ተከታታይ የሆነ ለውጥ ማምጣት እና ወጪን በመቀነስ ትርፍን መጨመር ላይ ትኩረት የሚያደርግ ፍልስፍና በመሆኑ በተለይ ሂደት ለውጥና የውጤት ተኮር የምዘና ስርዓት የተለየ ያደርገዋል ተባለ፡፡

በመንግስት ተቋማት ተግባራዊ ከተደረጉት የመሠረታዊ የአሰራር ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ከሁሉም ነገር በላይ ምቹና ጽዱ የሆነ የስራ አካባቢን በመፍጠር የሰራተኛውን ተነሳሽነት ማጎልበት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑም በገለጻው አጽንኦት ተሰጥቶታል፡፡ ስልጠናውን ሲሰጡ የነበሩ የካይዘን ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች ካይዘን ለተሻለ ነገር መለወጥ የሚል ትርጓሜ እንዳለው ጠቅሰው በስልጠናዎቹ ቀናት የተሰጡትን ትምህርቶች በፅንሰ ሀሳብ ደረጃ ብቻ መቅረት እንደሌለባቸው አስስበዋል፡፡ በተለይም በስልጠናው ላይ የተገኘው ሰልጣኝ ወደ የመጣበት ተቋም በሚመለስበት ወቅት ካይዘንን በስራ ቦታው ተግባራዊ ማድረግ እንደሚኖርበትና የተገኘውን እውቀት ወደ ሌሎች በማሸጋገር ለሀገራዊ ስኬት የበኩሉን አስተዋፅኦ መወጣት እንደሚኖርበት አብራርተዋል፡፡

በአጠቃላይ በስልጠናዎቹ ቀናት የካይዘን አጀማመርና ምንነት፣ የካይዘን ማስተግበሪያ ቴክኒኮች፣ የብክነት ዓይነቶች፣ የብክነት አወጋገድ፣ የችግር መፍቻ መሳሪያዎች፣ የጥራት መቆጣጠሪያ ቴክኒኮች፣ መመዘኛ መስፈርት በተሰኙት አርእስቶች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
ሰልጣኞች በበኩላቸው ኤጀንሲው ይህን መሰል ስልጠና ማዘጋጀቱ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው የሰለጠነውን ባለሙያ በተጨባጭ ስራ ላይ ማዋሉን መከታተል አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በ1950ዎቹ በአሜሪካ ፕሮፌሰሮች አማካኝነት የተጀመረው የካይዘን ፍልስፍና ከ40 ዓመታት በፊት በጃፓን ስራ ላይ ውሎ ውጤታማ መሆኑን ከዚህ በመነሳትም አገራችን ካለችበት ኋላ ቀርነት ተላቃ የተሻለ ኢኮኖሚን ለመገንባት ወሳኝ መሆኑንም ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
_________________________________________________
በ2006 በጀት አመት የተቀመረ የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ተሞክሮ //ሰነዱን ለማውረድ እዚህ ይጫኑ
_________________________________________________ የሰኔ ወር ዘገባዎች
- የማኑፋክቸሪንግ መስክን ለማሳደግ የሚከናወኑ ተግባራት በጥናትና ምርምሮች የግድ ሊደገፉ እንደሚገባ ተገለፀ
- የኢንተርፕራይዞች የኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ ማህበራዊ ችግሮችን የመፍታት አቅምን እንደሚፈጥር ተገለፀ
- የካይዘን ፍልስፍናና የአሰራር መርሆችን በማስፋፋት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በየደረጃው ተጠቃሚ ማድግ እንደሚገባ ተገለፀ
- በምሩቃን የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ የሚያተኩር ውይይት ተካሔደ
- የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ የልማት ሠራዊት ግንባታ አፈፃፀም የምክክር መድረክ ተካሄደ

_________________________________________________

የ2006 ሁለተኛው ዙር የሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተከፈተ

 የ2006 በጀት ዓመት ሁለተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚብሽንና ባዛር “የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን የምርት ጥራትና ምርታማነት በማሳደግ የኢንዱስትሪ ሽግግሩን እናፋጥናለን!” በሚል መሪ ቃል ግንቦት 25 2006ዓ.ም በፌዴራል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከፈተ፡፡ ኤግዚቢሽንና ባዛሩን በይፋ የከፈቱት የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደሳለኝ አምባው እንዲህ አይነቱ ኤግዚብሽንና ባዛር ከገበያ ትስስርና ከተሞክሮ ልውውጥ ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው እንደመሆኑ መጠን ውጤታማ ኢንተርፕራይዞችና የፈጠራ ባለቤቶች የተሻለ ገበያና ልምድ እንዲያገኙ በሁሉም የሀገራችን ክልሎች ሊተገበር የሚገባው ስራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ኢንተርፕራይዞቻችን ከደንበኞቻቸው፣ ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር እንዲገናኙና በስራዎቻቸው ዙሪያ እንዲመክሩ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባውም ሚኒስቴር ዴኤታው አስገንዝበዋል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገ/መስቀል ጫላ በበኩላቸው ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስርን ለመፍጠር ኤጀንሲው ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል እንዲህ አይነቱ ኢግዚቢሽን እና ባዛር በአመት ሁለት ጊዜ ማዘጋጀት እንደሚገኝበት ጠቅሰው ባለፉት አመታት በተዘጋጁት ኤግዚቢሽን እና ባዛሮችም በርካታ በማምረት ላይ የተሰማሩ የሀገራችን ሞዴል የጥቃቅንና አነስተኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን በማስተዋወቅና በመሸጥ ተጠቃሚ ለመሆን ብሎም እርስበርስ ተሞክሮ ለመለዋወጥ አጋጣሚ ለመፍጠር አስችሏቸዋል ብለዋል፡፡

የፋሲሊቴሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በቀለ መንግስቱ በኤግዚቢሽኑ መክፈቻ ላይ ባቀረቡት ንግግር በአመት ሁለት ጊዜ በፌዴራል ደረጃ የሚዘጋጀው ይህ የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ዋናው አላማው ኢንተርፕራይዞችን ክልላዊ ፡ሀገራዊ እና አለምአቀፋዊ ገበያ ዘለቄታዊ በሆነ መንገድ በምርት ጥራት፣ በምርታማነት እና በዋጋ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን የእርስ በርስ የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበትና ከምርት ተጠቃሚዎቻቸው ጋር የሚገናኙበት የትውውቅ መድረክ መፍጠር ነው፡፡

ኢግዚቢሽኑ ከ15ሺህ በላይ በሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እና በአካባቢው ህብረተሰብ እንደሚጎበኝ እና ብር 7.5 ሚሊየን የሚገመት የገበያ ትስሰር የፈጠራል ተብሎ እንደሚጠበቅም አቶ በቀለ መንግስቱ ገልፀዋል፡፡

የሁለተኛ ዙር ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተሳታፊ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች በቆይታቸው ወቅት በምርታማነትና በምርት ጥራት ፡በሽያጭ ክህሎት በዋጋና በዲዛይን የእርስ በርስ ተሞክሮ ልውውጥ እንደሚያደርጉ ፤አዳዲስ ደንበኞችን እንደሚተዋወቁ ፡የነባር ደንበኞቻቸውን አስተያያት እንደሚቀበሉ ፤ሽያጭ እንደሚያከናውኑ እንዲሁም ምርቶቻቸው ወይም አገልግሎታቸው እና በገበያው ፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት እንደሚለዩ በተጨማሪም በኢኮኖሚው እድገት ምክንያት እያደገ የሚሄደውን የደንበኞች ተለዋወጭ ፍላጎት እንደሚያጠኑ ይጠበቃል፡፡ኢግዚቢሽኑ ከግንቦት 25 እስከ ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ለ7 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡

 

Important Links:

History:

Etege Menen

Empress Menen Asfaw wife and consort of Emperor Haile Selassie I of Ethiopia wearing Ethiopian handmade cloths.

Advertisement

advertisement .